fbpx
מפרץ אילת 2/3 אריאל
054-6314141

סבא מקוננט בלטה ז”ל

አውራ የሌለው ንብ ተበታትኖ ይኖራል
ከዳንኤል በለጠ
ይህ የአባቶቻችን አባባል ሲሆን በአሁኑ ስዓት እኛ የኢትዮጵያ ይሁዲወች ያለነበትን አስቸጋሪ ጊዜ ሊጠቅስ የሚችል ጥቅስ ነው። ድሮ በስደት እያለን ታላላቅ ወገኖቻችን፣ታሪክን በመተርክ፣ባህልን በመጠበቅ፣ሃይማኖትን በመጠበቅ፣በተቻለ መጠን አገሩን መስለው ይኖሩ ነበር። ባህልና ታሪክ ለሰው ልጅ ዋና ቅርሶቹ ናቸው፡: ለመግቢያ ስል ባህልና ታሪክ ምን እንደሆኑ ለመግለጽ እወዳለሁ:፡ ታሪክ ማልት የአንድ ህብረተሰብ ወይም ህዝብ ምንጭ ማለት ነው:: ይህ ታሪክ የዚህን ህዝብ አመጣጡን፣አሰፋፈሩን፣አኗኗሩን ወ.ዘ.ተ የሚገልጽበት ታላቅ ሃብቱ ነው። ባሀል ደግሞ ሕብረተሰቡ ወይም ሕዝቡ ከሊሎች ሕዝቦች የሚለይበት የአመጋገብ፣
የአነጋገር፣የአለባበስ ፣ የስነመግባር ዘይቤ ነው። ይህ በመሆኑ ሕዝቦች በታሪካቸዉና በባህላቸው ኮረተው በራሳቸው ተማምነው ማንነታቸውን መግልጽ ይችላሉ።ታሪኩና ባህሉ እንዲሁም ሓይማኖቱ የሕዝቡ መለያ ምልክቱ ሲሆን የወደፊቱን ህይወቱን በቀና መንገድ ሊመራበትና በደረሰበት የስልጣኒ ዘመን ሁሉ ታሪኩን ባሀሉንም ሆነ ሃይማኖቱን በመጠበቅ ራሱን የሚያዋህድበትን
መንገድ ያገኛል፣ይህም በመሆኑ ታላቅ እንክብካቢ ያደርግላቸዋል፣ይህም ካለፉት ሆነ በዘመኑ ካሉት ታላላቅ የሃይማኖት መሪወች እንዲሁም እድሚና ዘመን ካሰተማራቸው ታላላቅ ሰወች ጥበብንና ጠቃሚ ምክሮችን በመቀበል በራሱ የሚተማመን፣ በራሱ የኮራ፣ደፋር፣ጠንካራ፣ትጉ የሆነ ማህበረሰብ መፍጠር ይችላል። ከዚህም በተረፈ ለሌላዉም ምሳሌ ይሆናል፣ይህን በተመለከተ “ታሪክ የሊለው ሰው ህይወቱ ባዶ ነው” ይባላል ይህ ታሪክና ባህል ከተግባር ላይ እንዲዉልና ከትውልድ ወደ ትውልድ
እንዲተላፍ ይህን ጥቅስ አዉቀው ታሪካቸዉን ተመክተው የሚሄዱ መሪወች ያስፈልጉናል፡፡ መሪ ማለት አስተማሪ ማለት ነው ፣ አስተማሪ ማለት ደግሞ ሃ ሁን የሚያስተምር ሳይሆን መንገድ የሚመራ ማለት ነው። እንደነዚህ አይነት መሪም በነዚህ ነገሮች በመኩራትና በመመርኮዝ ከሊላው ህዝብ ጋር ሊያዋህዱና ሊያስማሙ የሚችሉ መንገዶችን ይፈጥራሉ።
ታሪክና ባህል የተገንቡት እንደ እህል ማጠራቀሚያ ጎታ እየተደራረበ ነው፡እያንዳነዱ ድርቭ የሚቆመው ከታችኛው ላይ ነው የታችኛውም ደግሞ የላይኛዉን አስማምቶ ተሸክሞ ለላይኛው ያመቻቻል የላየኛውም እንዲሁ።
ስለዚህ የ 2500 ዓመት የሃይማኖት አጠባበቅ ፣በየዘመኑ የነበሩ የተለያዩ ታላላቅ መሪወቻችን ታሪክ እንዲሁም በየጊዝየው የነበሩት ችግር፡መከራ፡ስቃይ፡እስራት፡ስቅላት፣እልቂት፣ርሃቭ ብሎም ብዙ ዘመን ሲሳሳትና ሲመኝላት ከነበረችው ቅድስት እየሩሳለም ያደረገዉን ጉዞ ጠብቆ ለትዉልድ በታሪክ መዝግቦ እንዲተላለፍ ማድረግ ግዲታ ይሆንበታል።
ይህ ካልሆነ ግን ድቅድቅ ባለ ጨለማ በግምት መራመድ ማለት ነው፣ ምን እንደሚያገኘው፣ የት እንደሚወድቅና ፣ሾህ
ይዉጋው አይዉጋው ባጭሩ ምን ዓይነት አደጋ እንደሚያገኘው ባለማወቅ የግምት ጉዞን ይጓዛል። ትዉልዱም የገበታ ውሃ በመምሰል ወደዚህና ወደዚያ ወለል ወለል በማለት ረግቶ ሊቀመጥ አይችልም ። ስለዚህ ታላላቅ የታሪክ አባቶቻችን እንደነበሩን ሁሉ ዛሪም የእነሱን ምሳሌ ይዘን መሂድ ስንችል፣ መንገዱ ብርሃን እየሆነ ለሚቀጥለው ትዉልድ መንገድ እየከፈትነ እንሄዳለን ማለት ነው ።አባቶቻችን እንደተምር ዛፍ ይመሰላሉ፡የተምር ዛፍ ረዥም ነው ብዙ ቅጠልም የለውም፣ጽሃይ በሆነ ጊዜ ረዢም በመሆኑ ጥላው ከታች አይታይም ግን እራቅ እያልነ ስንሄድ ጥላው ከሩቅ ይታያል አባቶቻችንም እንዲሁ አሁን ከእኛ ጋር እያሉ ጥቅማቸው አይታይም ሲልዩን ግን በህይወታችን ላይ ትልቅ ጉድለት ይታያል ጊዜው እየራቀ በሄደ ቁጥርም እንዴት ለኛ ኩራት፡ትምህርት፣መመኪያ፡ትልቅ መሪወች እንደሆኑ እንረዳለን ፣ከዚያም በመቆርቆር ያን ጊዜ የት ነበርኩ? እንዴት ይህን አልጠየኩም? ለምን አላዳመጥኩም? የሚሉ ጥያቄወች ይመጡና ሲቆጩን ይኖራሉ።

————————-
דבורים שאין להם מ לכהוד מפוזרים לעד זו אמירה מאבותינו, פסוק שיכול להצביע על התקופות הקשות בהן אנו נמצאים בעמדתם של יהודי אתיופיה. בזמן הגולה, האנשים הגדולים שלנו חיו ככל האפשר, מספרים את הסיפור, שמרו על התרבות, שמרו על הדת, ככל האפשר. תרבות והיסטוריה הם אחד הממצאים העיקריים למין האנושי: ברצוני לתאר על מה עוסקים תרבות והיסטוריה. זהו עושרו הגדול המספר את סיפורם של בני האומה הזו, התיישבותה, אורח חייהם וכו ‘. בהלה מספקת גם תזונה, המייחדת את החברה או האנשים מבני עמים אחרים.
זו מטאפורה של דיבור, לבוש, התנהגות. בגלל זה, אנשים גאים בהיסטוריה ובתרבות שלהם ויכולים לבטא את זהותם וזהותם העצמית. הוא ימצא דרך, וזה יהפוך אותם לנכס גדול, אחת המסורות הדתיות הגדולות של פעם ושל ימינו
מנהיגים יכולים גם ליצור קהילה סומכת עצמית, גאה בעצמה, חזקה, עובדת קשה על ידי קבלת החוכמה והטיפים מהגברים הגדולים שלימדו אותם. מעבר לזה דוגמא נוספת, במקרה זה נאמר כי האיש שאין לו היסטוריה ריק.
אנו זקוקים למנהיגים שיודעים את הפסוק הזה כדי להעביר אותו. מנהיגות פירושה מורה, ומורה פירושו שהוא מלמד, ולא את הדרך בה הוא מלמד. בגאווה וגאווה שכאלה, מנהיגים אלה יוצרים דרכים להשתלב ולהסתגל לקהל הרחב. ההיסטוריה והתרבות פותחו כגרעינים
מסד הנתונים לאחסון חופף, כל אחד מהאינטרנט נעצר בתחתיתו ובחלקו התחתון נושא את המתאם העליון ומייעל את החלק העליון, ואילו השני אינו עושה זאת. לכן חובה שהשמירה הדתית בת 2500 שנה, ההיסטוריה של מנהיגינו הגדולים בכל הגילאים ותלאות תקופתו תישמר בחיים מכאב הכלא, הטבח, המדבר והגעגוע לירושלים.
אם לא, פירוש הדבר להסתובב בחושך החושך, את מה שהוא מוצא, איפה הוא נופל, להילחם בסערה מסע קצר של ספקולציות, מבלי להבין איזו סכנה הוא מהווה. הילד אינו יכול לשבת בנוחות על הרצפה, כמו מי שולחן. לכן, כפי שיש לנו אבותיהם הגדולים, זארם ככל שאפשר לקחת את הדוגמא שלהם, אנו נפתח את הדרך לדור הבא, והדרך תהיה קלה.
עץ הדקל ארוך ואין בו הרבה עלים, כאשר השמש ארוכה, הצל אינו נראה מלמטה, אך כאשר אנו מתרחקים, הצל מופיע רחוק מאיתנו, ואבותינו אינם רואים אותנו יותר. אנו מבינים שהם מנהיגים גדולים, ואז איפה הייתי בזמן הריקבון? איך לא ביקשתי את זה? מדוע לא הקשבתי? השאלות באות וחיים כשאנחנו מתחרטים.

אהבתם, תנו לייק ושתפו

One Response

  1. babush הגיב:

    געגועים לסבא דג׳נה היקר
    זכר צדיק לברכה

כתיבת תגובה

האימייל לא יוצג באתר. שדות החובה מסומנים *